2018 Mid Exit Exam Registration
#MoE #ExitExam
ትምህርት ሚኒስቴር በጥር ወር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ይሰጣል። ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይቆያል።
እነዚህ ተማሪዎች በተቋም ደረጃ ምዝገባቸውን በተጠቀሱት ቀናት አድርገው መረጃቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል በመክፈል፥ የከፈሉበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ ከነሙሉ ስማቸው ለየትምህርት ክፍላቸው መላክ ይጠበቅባቸዋል።
የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት ደግሞ በራሳቸው እንደሆነ ተገልጿል።
ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ምዝገባቸውን
https://exam.ethernet.edu.et ላይ ማከናወን ይችላሉ።